በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉንና ንብረት ላይ ጉዳት መደረሱን ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ኡባህ አደም ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት ፤ ትናንት እኩለ ቀን አካባቢ ለጊዜው ባልታወቀ ሁኔታ የተነሳው የእሳት ቃጠሎ በአንድ ህንፃ ላይ ነው።
በአደጋው የአንድ ህጻን ህይወት ሲያልፍ በህንጻው ውስጥ የሚገኙ ክፍሎች፣ ፍራሾችና ሌሎች ንብረቶች ላይ ጉዳት መድረሱን አስታወቀዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ተጎራባች ከሆነው ገንደ ተስፋ አካባቢ ህጻናት ወደ ዩኒቨርሲው በአጥር ዘልለው በመግባት እንደሚጫወቱ አስታውሰዋል፡፡
እንደ ዶክተር ኡባህ ገለጻ የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን የእሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከያና መቆጣጠሪያ ዲቪዥን ፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞችና የአካባቢው ማህበረሰብ ባደረጉት ርብርብ እሳቱ የከፋ ጉዳት ሳያስከትል በቁጥጥር ሥር ማዋል ተችሏል፡፡ የደረሰው አደጋ በመማር ማስተማሩ ተጽዕኖ እንደማይኖር ተናግረዋል።
የአደጋውን መንስኤ የፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቡድን ማጣራት መጀመሩን አመልክተው በዩኒቨርሲቲው የተዋቀረው ኮሚቴ ደግሞ የወደመውን ሃብትና ንብረት መጠን እየለየ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *