“Our true nationality is mankind.”H.G.

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዘጠኝ ወራት 13 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር አተረፈ -ከወጪ ንግድ 2 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 13 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡ የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 55 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል፡፡

ባንኩ ተደራሽቱን ለማስፋት ተቀማጭ ገንዘብን በማሳደግ ተጠቃሚ ደንበኞችን በማፍራት የመንቀሳቀሻ ገንዘብን በማሳደግ ረገድ አመርቂ ስራ መስራቱንም ነው ያስታወቀው፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን እያደረገ ያለውን ተሳትፎ እያጠናከረ መሆኑንም ፕሬዝዳንቱ ጠቅሰዋል፡፡

በቀጣይም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚያደርገውን እንቅስቃሴና  ቅርጫፎችን ለማሳደግ ጠንክሮ እንደሚሰራ ማስታወቁን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

 

በዘጠኝ ወራት ውስጥ ከወጪ ንግድ 2 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ

በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ከወጪ ንግድ 2 ነጥብ 9 ቢሊየን ለማግኘት ታቀዶ 2 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር መገኘቱ ተገለፀ፡፡
የወጪ ንግድ ገቢ አፈፃፀሙ ከተያዘዉ ዕቅድ አንፃር 84 በመቶ ሲሆን ከ2012 ዓ.ም ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ17 በመቶ ብልጫ አለው ነው የተባለው፡፡
በዚህም በዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀሙ በግብርና 84 በመቶ ፣ በኢንዱስትሪ 72 በመቶ፣ በማዕድን ዘርፍ 95 በመቶ ማሳካት መቻሉ ተገልጿል፡፡
በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ክትትል ከሚደረግባቸው የግብርና ምርቶች 674 ነጥብ 3 ሚሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 745 ነጥብ 9 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡
በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ክትትል ከሚደረግባቸው የግብርና ምርቶች በበጀት ዓመቱ የዘጠኝ ወር አፈፃፀም ከዕቅድ አንፃር 110 በመቶ ሲሆን ከ2012 ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ 46 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ብልጫ አሳይቷል መባሉን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Share and Enjoy !

0Shares
0
0Shares
0